የወላጅ መምህር ማኅበር (PTA) እና የድጋፍ ሀብቶች

የሲያትል ምክር ቤት PTSA

የሲያትል ምክር ቤት PTSA አርማ

“እያንዳንዱ ልጅ። አንድ ድምፅ።”

የሲያትል ምክር ቤት PTSA በሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ በርካታ PTAዎችንና PTSAዎችን ይወክላል። ለPTAዎችና ለወላጆች ድጋፍና ሀብቶችን ያቀርባል።

የዋሽንግተን ግዛት PTA

የዋሽንግተን ግዛት PTA አርማ

“ራዕያችን የእያንዳንዱ ልጅ አቅም እውን እንዲሆን ነው”

በ1905 የተቋቋመው WSPTA በዋሽንግተን ግዛት ትልቁ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ከ80,000 በላይ አባላትንና ከ830 በላይ PTAዎችን ይደግፋል። ተልዕኮው ለሁሉም ልጆች ትምህርት ጠንካራ ተሟጋች መሆንና ቤተሰቦችን፣ ትምህርት ቤቶችንና ማኅበረሰቦችን የሚደግፉ ሀብቶችን ማቅረብ ነው።

ብሔራዊ PTA

የብሔራዊ PTA አርማ

“እያንዳንዱ ልጅ። አንድ ድምፅ።”

በ1897 የተጀመረው ብሔራዊ PTA በአሜሪካ ትልቁና ጥንታዊው የሕፃናት ተሟጋች ማኅበር ነው። ብሔራዊ PTA በመላው አሜሪካ ቤተሰቦችንና ማኅበረሰቦችን በማብቃት የእያንዳንዱን ልጅ አቅም እውን ለማድረግ ቁርጠኛ ነው። የPTA ዋና እሴቶች፦ ትብብር፣ ቁርጠኝነት፣ ብዝኃነት፣ መከባበርና ተጠያቂነት ናቸው።